የአማርኛ ጽሁፎችን ለመተንተን የሚጠቅሙ አጫጭር ፕሮግራሞችን የያዘ በፓይተን ፕሮግራም ቋንቋ የተጻፈ ስብስብ ነው።
በስብስቡ ውስጥ የተካተቱት፡
፩፡ መሰረታዊ የፓይተን ፕሮግራም ቋንቋ ክለሳ
፪፡ በአንድ ጽሁፍ ወይም መጽሀፍ ውስጥ ስንት አረፍተነገራት ወይም ቃላቶች እንደሚገኙ ለመለየት የሚያስችል ፕሮግራም።
፫፡ በአንድ ጽሁፍ ወይም መጽሀፍ ውስጥ የሚገኙ ተደጋጋሚ ቃላቶችን ለመለየት የሚያስችል ፕሮግራም።
፬፡ በጽሁፍ ውስጥ ተፈላጊውን ቃል የያዙ አረፍተነገራትን ለይቶ በማውጣት ለሚፈለገው ተግባር ማዋል።
ለዚህ ትንተና ይረዳ ዘንድ የአቤ ጉበኛ መጽሐፍ የሆነውን አልወለድምን እንጠቀማለን። መጽሐፉን እኔም ከድረ-ገጽ ላይ ነው ያገኘሁት። ውሂብ በሚለው አቃፊ አኑሬዋለሁ።